|
የምናበረክታቸው የ አገልግሎት አይነቶች SERVICES IN KINDቤተ ክርስቲያናችን ልጆች ቋንቋና መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ያደረገ ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እንዲማሩ፣ በግዕዝና በአማርኛ እንዲዘምሩ ያደርጋል። አባቶቻችን ያቆዩንን የሰበካ ጉባኤ ሕግና ደንብ ተከትሎ ክርስትና ማስነሳት ፈልገው ገንዘብ መክፈል ለማይችሉ ኦርቶዶክሳዊያን ልጆቻቸውን በነጻ ያጠምቃል። ከዚህ ዓለም በሞት ለተሰናበቱ ሰዎች እንደ ኦርቶዶክስ ሥርዓት ጸሎተ ፍትሐት አድርሶ ይሸኛል፤ ሐዘንተኞችንም በቃለ ወንጌል ያጽናናል። በጋብቻ ለሚወሰኑ ወጣቶች ሰርጋቸው በጸሎት (በሥርዓተ ተክሊል)፣ በመዝሙርና በሥነ ግጥም አምሮና ድምቆ እንዲከናወን ያደርጋል። በቤተሰብ ውስጥ ለሚፈጠሩ ችግሮችና፣ እንዲሁም ልዩ ልዩ መጥፎ ገጠመኞችን መነሻ አድርገው በግለሰቦች ሕይዎት ላይ ለሚከሰቱ የሥነ-አእምሮ ችግሮች ማለትም፣ ጭንቀትና ዲፕረሽን ለገጠማቸው ሰዎች ነጻ የሆነ የምክር አገልግሎት ይሰጣል።
|
||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||
|
Copy right © 2009 Debre Selam St. Michael Ethiopian Orthodox Tewahedo Church 1710 Moorpark Ave. San Jose, CA 95128 - (408) 370-2144. All rights are reserved. |
||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||||